እኔ አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ እርሱ ከወዳጆቼ ሁሉ ይልቅ የቅርብ ወዳጄ ነው፡፡ እርሱ በጣም ደግና እውነተኛ ስለሆነ አንተም እንድትተዋወቀው እፈልጋለሁ፡፡ ስሙ ኢየሱስ ይባላል፡፡ እርሱ የአንተም ወዳጅ መሆን ስለሚፈልግ በጣም ድንቅ ነገር ነው፡፡ ስለ እርሱ ልንገርህ፡፡ የእርሱን ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትና የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ አለምና በአለም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ የሰማይና የምድር አምላክ ነው፡፡ እርሱ ሕይወትንና እስትንፋስን ለሁሉም ይሰጣል፡፡
Arabic
Bemba (Zambia)
Bengali
Chinese
Dutch
English
French
German
Haitian Creole
Hindi
Indonesian
Japanese
Karbi
Kazakh
Khmer
Kinyarwanda
Korean
Lingala
Malagasy
Mossi
Nepali (Macrolanguage)
Norwegian
Nyanja
Oromo
Persian
Plautdietsch
Polish
Portuguese
Punjabi
Rundi
Russian
Southern Sotho
Spanish
Swahili (Macrolanguage)
Swedish
Tajik
Telugu
Thai
Tonga (Zambia)
Turkish
Ukrainian
Uzbek
Vietnamese