መዳን

በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ልጅ ሲወለድ የህይወትን ጉዞ ይጀምራል፡፡ በሰማይ የሚኖር አምላክ ለታዳጊ ልጆች ልዩ መንገድን ያደርጋል፡፡ ይሄ መንገድ የየዋህነት፣ እራስን ወደ ማወቅ የሚያመጣ መንገድ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ላይ እናትና አባት ለልጆች ስለ ህይወት በማስተማር መሪዎች ናቸው፡፡ በመስቀለኛው መንገድ ፊት ቆመህ ምን ትመለከታለህ? ሁለቱን መንገዶች በደንብ አስተውላቸው፡፡ መጀመሪያ ላይ ሁለቱም መንገዶች አትኩሮትን የሚስቡ ናቸው፡፡ ቀረብ ብለህ ስታስተውል አንደኛው መንገድ ሰፊ ደግሞም ለመጓዝ ምቹና ቀላል እንደሆነ ታያለህ፡፡ ሌላንኛው መንገድ ጠባብ በተላያዩ ቦታዎች ኮሮኮንችና ዳገታማ የሆነ ነው፡፡ ሰፊው መንገድ ብዙ ብዙ ሰዎች የሚጓዙበት ነው፡፡ ጠባቡ ጥቂት ሰዎችን ብቻ ይዟል፡፡ ትክክለኛውን መንገድ መምረጥ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ጠባቡን መንገድ ቀረብ ብለህ ተመልከተው፡፡

English French Spanish

19 ጁላይ 2023 in  መዳን 5 minutes

ሁሉም ሰው ይህንን “እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” የሚለውን ጠቃሚ ጥያቄ እራሱን ሊጠይቅ ይገባዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ድነናል ብለው ቢያምኑም ኢየሱስ ግን ሲናገር “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴዎስ 7፥21) ብልዋል፡፡ ድነትን ለማግኘት ክርስቶስ ኃጢአታችንን ይቅር እንደሚለን ማመን አስፈላጊ ነው፡፡ ከዛም ኃጢአታችንን መናዘዝ፣ በቅድስና መኖርና አንዳችን አንዳችንን በመውደድ በፍቅር ልንኖር ይገባል፡፡ በዚህ ዘመን የተለያዩ ኃይማኖቶች የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያስተምሩ ሲሆን ሊጠየቅ የሚገባው መሰረታዊ ጥያቄ ግን “እውነት የትኛው ነው?” የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ “ዳግም መወለድ” ማለት ምን ማለት ነው? ዳግም መወለድ የሚያስፈልገው ለማን ነው? ንስሐ እምነትና መታዘዝ

Bemba (Zambia) English Hindi Kazakh Norwegian Nyanja Romanian Spanish Swahili (Macrolanguage) Tonga (Zambia) Ukrainian

19 ጁላይ 2023 in  መዳን 4 minutes

የሰው ልጅ ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር ፊት በኃጢአቱ ወንጀለኛ ሆኖ በመገኘቱ ሞት እንደተፈረደበት ታውቃለህ? ከዚህ የዘላለም ሞት ፍርድ አምልጦ ለዘላለም ይድን ዘንድ የእግዚአብሔርን ምህረት መቀበል አለበት፡፡ ከዘላለም ሞት አንፃር ምህረት ማለት እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሊቀበል ለሚገባው ፍርድ ይቅርታን ሲያደርግ ነው፡፡ ምንም እንኳ ድነት ነጻ የማይከፈልበትና በስራችን የምናገኘው ባይሆንም እግዚአብሔር ግን ምህረቱን ለሰው ልጅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አይደለም የሰጠው፡፡ እግዚአብሔር ምህረት የሚደርግበት ቅድመ ሁኔታ ንስሐ ነው፡፡ ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋል ኃጢአት ያለያያል ንስሐ፣ የእኛ ድርሻ

Bengali Cebuano English French Hindi Kazakh Nepali (Macrolanguage) Nyanja Rundi Russian Spanish Tagalog Tonga (Zambia) Ukrainian

19 ጁላይ 2023 in  መዳን 4 minutes

የዮሐንስ ወንጌል 10፡ 1-18 አንድ ሰው ሲጠራህና የሚጠራህ ሰው ድምጽ ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ለማወቅ ግራ ተጋብተህ ታውቅ ይሆን? ወይም ብዙ ጫጫታ መካከል ከመሆንህ የተነሳ የሚጠራህን ሰው ድምጽ ለመስማት ተቸግረህ ታውቅ ይሆን? አድምጥ! አንድ ድምጽ እየጠራህ ነው፡፡ አዎ አንተን! አንተ ማን ነህ? ስምህ ማን ነው? ከየት ነው የመጣኸው? የት ነው ምትኖረው? ወዴትስ እየተጓዝክ ነው? የምትኖርበትን አካባቢ ስም ታውቃለህ፡፡ ድነገትም ከምትኖርበት አካባቢ ርቀህ ተጉዘህ አታውቅ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የምትኖርበት አካባቢ የአንድ አገር አካል፤ አገራት ደግሞ የአለም አካል እንደሆኑ ታውቃለህ;፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ከዚያን ግዜ ጀምሮ ብዙ ልጆች ተወልደዋል፡፡ ብዙ ሰውችም ሞተዋል፡፡ እግዚአብሔር በእርግጥ ማወቅ ትፈልጋለህ? አዎ! በርግጥም ማወቅ ትፈልጋለህ፡፡ ውስጥህ በርግጥም ማወቅ ይፈልጋል፡፡

Arabic Bengali English French Kazakh Mongolian Mossi Nepali (Macrolanguage) Norwegian Persian Portuguese Romanian Rundi Russian Southern Sotho Spanish Swedish Tagalog Tajik Thai Ukrainian Urdu

19 ጁላይ 2023 in  መዳን 5 minutes

መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ብዙ ጊዜ “በግል መዳናችንን ማስረገጥ እንችላለን ወይስ አንችልም?” ብለው ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስ ይሰጠን ይሆን? አንድ ሰው ኃጢያቱ ይቅር እንደተባለለት ያውቅ ይሆን? ወይስ ለማወቅ የፍርድ ቀን እስኪመጣ መጠበቅ ይኖርበታል? ይህን ወሳኝ ጥያቄ ለመመለስ እስከዚያን ቀን መቆየቱ አለመታደልና በጣም አደገኛ ውሳኔ ነው፡፡ አዎን፤ የፈለገ ሰው ማወቅ ይችላል፡፡ ጌታም ስለመዳናችን እርግጠኛ እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ” (ማቴ. 11፥28) እያለ ጥሪውን እያቀረበልን ነው፡፡ በዮሐ.3፥16 “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን (ኃጢያተኛውን፤ ሁሉንም) እንዲሁ ወዶአልና” ሲል ይነግረናል፡፡ ሰው ሁሉ ከፍጥረቱ ኃጢያተኛ በመሆኑ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ከማድረግ ጎድሏል፡፡

Arabic Bengali English French Hindi Spanish

30 ማርች 2020 in  መዳን 3 minutes