ዛሬ በዓለማችን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ልባቸው የታወከና የተጨነቀ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ምክንያቱ ምንም ቢሆን ምን እግዚአብሔር አዋቂ አማላክ እንደሆነ ልናምን፣ የተጨነቁ ልቦች ወደ እርሱ እንዲመጡ ጥሪውን እያቀረበና ሰላምን ሊሰጣቸው እየጠበቀ እንደሆነ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ይወድሀል፣ በልብህም ውስጥ ሊኖር ይሻል፡፡
በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሰው ልብ የሚያሳየው ሰው የሚወደው ነገር ሁሉ መቀመጫ የሆነውን ወይም “እውነተኛ አንተነትህ” ነው፡፡ የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የሚመነጩት ከልብህ ነው፡፡
ሰውን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በደስታና እያገለገለው በውቧ ኤደን ገነት እንዲኖር ነበር፡፡
ነገር ግን የእግዚአብሔርን እቅድ የሚያበላሽ ነገር ተፈጠረ፡፡ ሰይጣን ብለን የምንጠራው ዲያብሎስ እግዚአብሔርን አጥብቆ ይጠላል፡፡ ሰው እንዲጠራጠር ምክንያት ፈጠረና እግዚአብሔርን እንዳይታዘዝ አደረገው፡፡ በዚህም ምክንያት የሰው ልብ ክፉና በኃጢአትን የተሞላ ሆነ፡፡ ከደስታዎች ሁሉ በላይ የሆነውን ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የማድረግን ስጦታ የሰው ልጅ አጣ፡፡ የሰው ልብ ተንኰለኛና እጅግም ክፉ ሆነ (ኤርምያስ 17፥9)፡፡ ሰውም ከእግአብሔር ጋር ተለያየ፡፡
እግዚአብሔር ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ ልጁን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ለሰው ልጅ ሁሉ ኃጢአት እንዲሞት ላከው፡፡ ለሰው ሁሉም አዲስ ተስፋን ተሰጠ፡፡ እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ መኖር ይፈልጋል፡፡ አንድ ቀንም የዳኑት ሁሉ ገነት በተባለው ውብ መኖሪያው ከእርሱ ጋር እንዲኖሩ ይወስዳቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ምንም ኃጢአት ወደዚህ ስፍራ እንዳይገባ ወስኗል፡፡
ማንኛውም የእግዚአብሔርን ፍቃድ የሚቃረን ሀሳብ፣ አመለካከት፣ ድርጊት እና እምነት ሁሉ ኃጢአት ነው፡፡ እነዚህ ኃጢአት ደግሞ የሰውን ልብ ያጎድፋሉ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ውጪያዊ ድርጊት ብቻ ሳይሆን ልብንም ጠልቆ ያያል፡፡ ከእግዚአብሔር ፊት የተሰወረ ምንም ነገር የለም፡፡ በየትም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከኃጢአታቸው ንስሐ እንዲገቡ ያዝዛል (የሐዋርያት ሥራ 17፥13)፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ችላ ከተባለ ያለታዘዘ ሰው ሁሉ ሲኦል በተባለው የእሳት ባሕር ውስጥ ይጣላል (ማቴዎስ 25፥41)፡፡
ከኃጢአታችን ተጸጽተንና ተናዘን ይቅርታን ልናገኝ ይገባል፡፡ ያን ጊዜ እግዚአብሔር እርሱን የሚወድ እና የሚያገለግለውን ልብ በውስጣችን ይፈጥርልናል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ ከውጪ ሆኖ የሚወቅሰን ሳይሆን ወደ ልባችን በመግባት አጽናኛችንና መሪያችን ይሆናል፡፡ በመጨረሻም በምድር ያለ ቆይታችን ሲጠናቀቅ እግዚአብሔር ወደ እርሱ ይቀበለናል፡፡
የኃጢአተኛ ሰው ልብ
የኃጢአተኛ ሰው ልብ በዚህ አለም ገዢ የሚመራ ልብ ነው፡፡ የዚህ ዓለም ገዢ የኃጢአተኛን ሰው ልብ በተለያዩ ክፉ መናፍስቶቹ ቁጥጥር ስር እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ከእነዚህ ክፉ መናፍስቶች መካከል ትዕቢትና ራስ ወዳድነት ይገኙበታል፡፡ ሰይጣን በዚህ ኃጢአተኛ ሰው ልብ ዙፋን ላይ እንደተቀመጠ በምስሉ ላይ ይታያል፡፡ ጣኦስ (ፒኮክ)፣ አንበሳ፣ አሳማ፣ እባብ አና ሌሎች የተለያዩ እንስሳት በኃጢአተኛ ልብ ውስጥ ያለን ባዶነት፣ አመጸኛነት፣ ርኩሰት፣ አጭበርባሪነት እና ሌሎች ክፉ ባህርያትን ይወክላሉ፡፡ ከኃጢተኛ ሰው ልብ ውስጥ የሚመነጩ መልካም ነገሮች እንኳ ከትዕቢትና የራስን ክብር ከመፈለግ ስለሚመነጩ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም፡፡
የኃጢአተኛ ሰው ልብ ሀፍረትና ውርደት መጨረሻው የሆነ ሰካራምነት፣ የዝሙት ምኞት፣ ክፉ ንግግር (ምሳሌ 23፥29-33) የሞላበት ሊሆን ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ቤተ መቅደሱ አድርጎ ሊጠቀምበት የሚፈልገውን የሰውን አካል (1ኛ ቆሮንቶስ 3፥16-17) የሚያዋርድና የሚያረክስ ሲጋራን የማጨስ ሱስ ብዙ ጊዜ የሚገኘው በኃጢአተኛ ሰው ልብ ውስጥ ነው፡፡
የስጋ ምኞት፣ ስርአት አልበኛነት፣ ዝሙት እና አመንዝራነት በተግባር እንኳ ባይሆን በሀሳብ መኖሪያቸው የኃጢአተኛ ሰው ልብ ነው፡፡ ኢየሱስ ሴትን አይቶ መመኘት ከእርስዋ ጋር ማመንዘር እንደሆነ በማቴዎስ 5፥28 ላይ አስተምርዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ ልብ ሀፍረተ ቢስ እና ኃጢአት በሞላባቸው ሰዎች ሕይወት ይደሰታል፡፡ ጭፈራ ቤቶች፣ ሲኒማና ቲያትር ቤቶች እና አጸያፊ ስነ-ጽሁፎች የኃጢአተኛን ሰው ክፉ ምኞት ከሚመግቡ አመጾች መካከል ጥቂቶቹ ኛቸው፡፡ “ዝሙትን የሚሠራ በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል”(1ኛ ቆሮንቶስ 6፥18)፡፡
ስስታምነት ከሰካራምነት ጋር የሚነጻጸር ክፍ ኃጢአት ሲሆን በብሉይ ኪዳን ሕግ ከባድ ቅጣትን የሚያስከትል በደል ነበር (ዘዳግም 21፥18-21)፡፡ እንደ ጫት፣ ሺሻ፣ ሀሺሽ፣ ማሪዋና እና ኮኬይን የመሳሰሉ ስሜትን የሚቀያይሩ እፆች ይህን ልብ ተቆጣጥረውት ሊሆን
የኃጢአተኛ ሰው ልብ
ይችላል፡፡ እንደዚህ ያሉ እፆች በአእምሮ ላይ ብቻ ሳይሆን በአካል እና በነፍስ ላይ የሚያደርሱት ጉዳት የከፋ ነው፡፡
ቁማር፣ ማጭበርበር፣ ስርቆት፣ ውሽት፣ ማታለል ለልብ ስብራት ይዳርጋሉ፡፡ እንደዚህ ያሉ ኃጢአቶች ብዙውን ጊዜ “ሁሉም ሰው የሚያደርገው ነገር ነው” በሚል የማታለያ ቃል ይደረጋሉ፡፡ “የተሳሳተ ነገር እያደረኩ አይደለም”፣ “እያደረኩ ያለሁት ነገር ማንም ሰው ላይ ጉዳት አያደርስም” ወይም “ሁሉም ሰው የሚያደርገው ነገር ነው” የሚሉ አባባሎች እነዚህን ኃጢአቶች ለማድረግ የሚቀርቡ ምክንያቶች ናቸው፡፡
የሌሎች የሆነውን የራስ የማድረግ ምኞት በዚህ ክፉ ልብ ውስጥ ተጠንስሶ ያድጋል፡፡ የኃጢአተኛ ሰው ልብ ባለቤትነታቸው የሌሎች ሰዎች የሆኑ ነገሮችን አይቶ የራሱ ለማድረግ ይመኛል፡፡ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰው ልብ ሀሳብ ምድራዊ ሀብትን ማጋበስ ነውና የተመኛቸውን ነገሮች በተገቢም ይሁን ተገቢ ባልሆነ መንገድ የራሱ ለማድረግ ይተጋል፡፡ የእንዲህ አይነቱ ኃጢአት ሩጫ መጨረሻ በሉቃስ 16፥19-31 ላይ እንደሰፈረው ባለጠጋ ሰው አይነት ይሆናል፡፡ ይህ ሀብታም ሰው ከሲኦል ሆኖ የተቃጠለ ምላሱ በውሀ ጠብታ እንዲቀዘቅዝ ይለምናል፡፡
በምስሉ ላይ በኤሊ የተመሰለው ስንፍና፣ ግዴለሽነት፣ ስራንና የሚጠበቅበትን ነገር በአግባቡና በጊዜው ባለመስራት ለሌላ ቀን እና ሰዓት መቅጠር እና ቸልተኝነት በዚህ ልብ ውስጥ የሚገኙ ኃጢአቶች ናቸው፡፡ ይህ ልብ ስራን በመጥላት በእጆቹ ሰርቶ ከማግኘት ይልቅ የሌሎች የሆነውን የራሱ ለማድረግ ይመኛል (ምሳሌ 21፥25-26)፡፡
ጥንቆላ፣ መጭውን ጊዜ በኮከብ ቆጠራ መገመት (ሆሮስኮፕ)፣ መናፍስት ጠሪነት እና የመሳሰሉት ልምምዶች ከመንፈስ ቅዱስ የራቀን ልብ ለመምራት የሚያገለግሉ የክፉው ምሪቶች ናቸው፡፡ እንዲህ ያሉት ሰይጣናዊ ልምምዶች የኃጢአተኛ ሰው ልብን ወደ ባሰ ጨለማ ከመምራት ውጪ ምንም ጥቅም ስለሌላቸው እግዚአብሔር አጥብቆ ይጸየፋቸዋል (ኢሳይያስ 47፥12-15)፡፡
እንዲህ አይነት ልብ በውስጡ የያዘው ጥላቻ እና ጭካኔ ብዙ ጊዜ በክፉ ቁጣ አማካኝነት ይገለጣል፡፡ ቁጣ እና ያልተገባ ባህሪ የሚዘወተሩ ልማዶች ሲሆኑ ፍትህን በማስፈን ስም በቀለን ሲፈጽም ይስተዋላል፡፡ መዝሙር 37፥8 ላይ ራቅ፣ ተው በማለት እነዚህን ኃጢአት እንድናስወግድ ያዘናል፡፡ የኃጢአተኛ ሰው ልብ ባልንጀራውን እንደራሱ መውደድ አይችልም፡፡ ይህ ልብ መጥፎ ባህሪያቱን ለተወሰነ ጊዜ ሊቆጣጠራቸው ቢሞክርም ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን እነዚህ ክፉ ባህሪያት በሀይልና በአጥፊነታቸው መገላጣቸው የማይቀር ነው፡፡ ውጤቱም ሀዘን፣ የልብ ስብራት፣ ስቃይ ብሎም ሞት ሊሆን ይችላል፡፡ ቅናት፣ ክፋት፤ ምቀኝነትና የጥላቻ ስሜት ይህንን ልብ ተቆጣጥረው ለሌሎች ሕይወት የስቃይና የሀዘን ምክንያት እንዲሆን ያደርጉታል፡፡
ትዕቢት በግብዝነትና በእኔነት በኃጢአተኛ ሰው ልብ ውስጥ ያድጋል፡፡ ኃጢአተኛ ልብ የሌሎችን ስሜትና ደህንነት ችላ በማለት ለራሱ ምቾት ብቻ ይጨነቃል፡፡ በምድራዊ ክብር፣ የትምህርት ስኬት፣ ፋሽን፣ ቁሳዊ ይዞታ፣ ዝና፣ ተቀባይነት፣ እብሪት፣ አውቃለሁ ባይነት፣ የራስ ጽድቅ፣ ግላዊ መብት ራሱን ያስጌጣል፡፡ እንዲህ አይነቱ ልብ በቀላሉ የሚጎዳና የሚከፋ ሲሆን ቂመኛም ነው፡፡ በሌሎች ሰዎች እውቅና ካለተሰጠውና ካለተጨበጨበለት በዙሪያው ያሉትን ከመበጥበጥና ከመጉዳት ወደ ኋላ አይልም፡፡ በቤተሰባዊ ዝምድና ወይም የቀድሞ ቤተሰቦቹ በሰሩት ገድል ይታበያል፡፡ ስልጣን እና ሙገሳ ምኞቱ ናቸው፡፡ እርሱ ብቻ የሰራውን አጋኖ በማውራት የባልንጀሮቹን እርዳታና እገዛ ችላ ይላል፡፡ ትዕቢት ‘ግልጽ እና አግባብነት ያለው ሕይወት ኑሩ’ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርን ችላ ይላል፡፡ እራሱን በተለያዩ ምክንያቶች እያጸደቀ የሌሎችን ምክርና ተግሳጽ ወደ አለመስማት ያድጋል፡፡
ትዕቢት ከሰማይ የተጣለ ሲሆን ወደ እዚያ ስፍራ ደግሞ በፍጹም አይገባም፡፡ መጽሕ ቅዱስ አግዚአብሔር ትዕቢተኛ ዓይንን እንደሚጠላ ይነግረናል (ምሳሌ 6፥16-17)፡፡ የትዕቢት ምንጭ ሰይጣን ሲሆን መጨረሻው ደግሞ ሲኦል ነው፡፡ “ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል” (ምሳሌ 16፥18)፡፡ እግዚአብሔር ትዕቢትን ይጠላል ይቃወማልም፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል (1ኛ ጴጥሮስ 5፥5)፡፡
ኃጢአተኛ ሰው ህሊናውን ላለማዳመጥ ቢጥር ወይም ህሊናው ቢደነዝዝ እንኳ (1ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2) ከወቀሳው ማምለጥ አይችልም፡፡ ምንም እንኳ ህሊናው የሚለውን ቸል ቢልም ዝምታ እና ጸጥታ በሚሆንበት ጊዜ ወቀሳን እና ፍርድን ወደ ኃጢአተኛው ሰው በማምጣት ሰውየው ወንጀለኛነትና ፍርሀት እንዲሰማው ያደርጋል፡፡ በሕዝቅኤል 18፥4 ላይ “ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች” እንደሚል እግዚአብሔር ኃጢአተኛ ሰው ፍርድ እንደሚጠብቀው የሚናገርበት መንገድ እንዲህ ያለ ወቀሳን ወደ ኃጢአተኛ ሰው ህሊና በመላክ ነው፡፡
የኃጢአተኛ ሰው ልብ በአታላይ ጭፍንነት፣ በስንፍና እና በተጽእኖ መንፈስ ተወጦ በግልጽ የእግዚአብሔርን ፍቅር ይቃወማል፡፡ ወደ ዘላለማዊ ጥፋት የሚነዱት ተመሳሳይ ልብ ያላቸው ብዙ ሰዎችን እየተመለከተ ይጽናናል፡፡ እየተደሰተ ካለበት ኃጢአት ለመመለስን ንስሀ ለመግባት ወይም ከእስራቱ ለመፈታት አመቺው ጊዜ ነገ ወይም ሌላ ቀን እንደሆነ ያስባል፡፡ ንስሀ እንድንገባ ከሚያዘን መጽሐፍ ቅዱስ ፊቱን በማዞር የሌሎች ኃጢአተኞችን ምክር ይቀበላል፡፡ ሰይጣንም ያለምንም ርህራሄ አይኖቹ እውነትን እንዳያዩ ያሳውረዋል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቃል ሲቀርብ አንኳ ጠላት በተሳሳተ መንገድ ይመራዋል፡፡ ሔዋንን “እግዚአብሔር……አዝዞአልን?” በሚል ጥያቄ እንድትጠራጠር እንዳደረጋት እንዲሁ ዛሬም የኃጢአተኛን ሰው ልብ ያስታል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር “በእርሱ (በኢየሱስ) የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐንስ 3፥16) እያለ ለዚህ ኃጢአተኛ ሰው ልብ መናገሩን ዛሬም አላቆመም፡፡ አዎ፣ የታወከ ልብ ላለው ሰው ሁሉ ዛሬም እግዚአብሔር “ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም” (ዮሐንስ 6፥37) እያለ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ እና ንስሀ መግባት
በመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ ንስሀ በመግባት ሂደት ውስጥ እያለፈ ያለ የኃጢአተኛ ሰው ልብ ለእግዚአብሔር ፍቅርና ፍርድ ምላሽ መስጠት የጀመረ ልብ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ኃጢአተኛን ሰው ስለ ኃጢአቱ ሲወቅሰው፣ ሊመጣ ስላለው ፍርድ ሲያስጠነቅቀውና ለድነት ወደ ኢየሱስ እንዲመለስ ሲጋብዘው ይቆያል፡፡ ከዚህ ሰው ልብ ውስጥ ጸሎት ድምጽን በማውጣት እንኳ ባይሆን ከነፍስ በሆነ ጩኸት ወደ ጸጋው ዙፋን ይቀርባል፡፡ ኃጢአጠኛ ሰው ውጫዊው ገጽታው ሲታይ ነጻነት ያለው ቢመስልም ውስጣዊው ማንነቱ ግን በጨካኙ አስገባሪ የታሰረ ነው፡፡ የሰማይ አምላክም ይህንን ስቃይ ተመልክቶና እርዳታ ፍለጋ የምትጮህን ነፍስ ሰምቶ ምላሽን ይሰጣል (ዘጸአት 3፥7)፡፡ እንዲህ አይነቱ ልብ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሆነ ጸጋ ብርሀንን እና መረዳትን ይቀበላል፡፡ የሚቀበለው ብርሀን በቃሉ አማካኝነት ኃጢአቱን እንዲመለከት ሲለዳው የተቀበለው መረዳት ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል በእምነት እንዲቀበል ያግዘዋል፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ጭንቀትና ፍርሀት ከልቡ ይወገዳል፡፡
ይህ ኃጢአተኛ ልብ በእግዚአብሔር ፊት ማንነቱ መጥፎ መሆኑን ይረዳል፡፡ ለሚጠብቀውም የእግዚአብሔር ቁጣ ሊከፍለው የሚችለው አንዳች እንደሌለው ይገነዘባል፡፡ ከስንፍናው የተነሳ ቁስሉ