ሞራል

“እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ” (መዝሙር 51፡6) ታማኝነት የእውነተኛ ህይወት መገለጫ ባህርይ ነው፡፡ ታማኝነት በዋናነት የልብ ጉዳይ ነው፡፡ ታማኝነት ከኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መሰረታዊ መመሪያዎች አንዱ ነው፡፡ እግዚአብሔር የልብን ሀሳብና መሻት ያውቃል፡፡ እውነተኝነት ለእግዚአብሔር መሰረታዊ መርህ ነው ምክንያቱም እርሱ የእውነት አምላክ ነው (ዘዳግም 32፡4)፡፡ ሙሉ በሙሉ ታማኝ የሆነ ልባችንን በእርግጥም ይባርካል፡፡ የሚታወቅብህ ከመሰለህ እውነትን፤ ማንም ማያውቅብህ ከሆነ ግን ውሸትን ትናገራለህን? ሆን ብለህ ሰዎችን ወደ ተሳሳተ አመለካከት ትመራቸዋለህ? መክፈል እንደማትችል እያወቅህ እዳ ውስጥ ትገባለህ? ስትፀልይ ያለህበትን ሁኔታ በግልጽ ለእግዚአብሔር ትናገራለህ? እግዚአብሔር እንድታደርግ ያሳወቀህን ሁሉ በታማኝነት ታደርጋለህ? ለመጽሀፍ ቅዱስ አትተምሮዎች ታማኝ ነህ? በሰዎች ፊት ሆነህ እንደምትቀርበው ዓይነት ሰው ነህን?

ሞራል 4 minutes