የሱስ

በመጀመሪያ አለማችን ባዶ ነበረች፡፡ አሶች በባህር፣ ከዋክብት በሰማይ ላይ አልነበሩም፤ ባህርና ውብ አበቦች የሉም ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ነበር፡፡ እግዚአብሔር አስደናቂ እቅድ ነበረው፡፡ ውብ የሆነች አለምን ለመስራት አሰበ፡፡ እንዳሰበም ፈጠራት፡፡ እግዚአብሔር አለምን ሲፈጥር ከምንም ነው የሰራት፡፡ “…..ይሁን” አለ፤ ሆነም! ብርሀንን ፈጠረ፡፡ ወንዞችንና ባህርን፣ በሳር የተሸፈነች ምድርን፣ እንስሳትን፣ አእዋፋትንና ዛፎችን ሁሉ ሰራ፡፡ በመጨረሻ ሰውን ፈጠረ፡፡ ለፈጠረው ሰውም ሚስትን አበጀለት፡፡ ስማቸውም አዳምና ሔዋን ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሐር አዳምና ሔዋንን በጣም ይወዳቸው ነበር፡፡ ይኖሩበት በነበረበት በውቡ ገነት ሁልግዜ አመሻሹ ላይ እየመጣ ያነጋግራቸው ነበር፡፡ አዳምና ሔዋን እግዚአብሔር ከከለከላቸው ከአንድ ዛፍ በስተቀር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዲበሉ ተፈቅዶላቸው ነበር፡፡

የሱስ 3 minutes

ኢየሱስ የአንተ ወዳጅ እኔ አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ እርሱ ከወዳጆቼ ሁሉ ይልቅ የቅርብ ወዳጄ ነው፡፡ እርሱ በጣም ደግና እውነተኛ ስለሆነ አንተም እንድትተዋወቀው እፈልጋለሁ፡፡ ስሙ ኢየሱስ ይባላል፡፡ እርሱ የአንተም ወዳጅ መሆን ስለሚፈልግ በጣም ድንቅ ነገር ነው፡፡ ስለ እርሱ ልንገርህ፡፡ የእርሱን ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትና የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ አለምና በአለም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ የሰማይና የምድር አምላክ ነው፡፡ እርሱ ሕይወትንና እስትንፋስን ለሁሉም ይሰጣል፡፡ ኢየሱስ ወደ ምድር እንደ ትንሽ ሕጻን ልጅ መጣ፡፡ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት አባትና እናቱ ዮሴፍና ማርያም ነበሩ፡፡ እርሱ በጋጣ ተወልዶና በግርግም ተኝቶ ነበር፡፡