የወደፊት ሕይወት

በአሁኑ ወቅት ሕያው ነዎት፤ ይተነፍሳሉ፤ ከቦታ ቦታ ይንቀሳቀሳሉ፤ ስራዎንም ያከናውናሉ፡፡ እየኖሩ ያሉት ሕይወት በምቾት ወይም በችግር የተሞላ ሕይወት ይሆናል፡፡ ፀሀይ ትወጣለች ደግሞም ትጠልቃለች፤ በአንድ ስፍራ ህጻን ይወለዳል በሌላ ስፍራ ደግሞ አንዱ ይሞታል፡፡ ሕይወት በአጠቃላይ ጊዜያዊ ቅንብር ነች፡፡ ነገር ግን እርስዎ ከሞቱ በኋላ ወዴት ይሄዳሉ? ኃይማኖተኛ ሰው ቢሆኑ፤ ወይም ምንም አይነት ኃይማኖት ባይኖርዎ ይህንን መሰረታዊ ጥያቄ መመለስ ይኖርብዎታል፡፡ ምክንያቱም ሰው ሁሉ ከአጭር የምድራዊ ቆይታው በኋላ ወደ ዘላለም መኖሪያው ያመራልና (መክብብ 12፡5)፡፡ ግን ወዴት? የሚቀበሩበት የመቃብር ስፍራ ነፍሶን ማስቀረት አይቻለውም፡፡ በድንዎ በእሳት ተቃጥሎ ቢጠፋ፤ ነፍስዎን እሳት አይበላትም፡፡ በጥልቁ ባህር ውስት ገብተው ቢጠፉ፤ ነፍስዎ አትሰምጥም፡፡ ነፍስዎ በፍጹም አትሞትም! የሰማይ እና የምድር ሁሉ አምላክ