መዳን
መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ብዙ ጊዜ “በግል መዳናችንን ማስረገጥ እንችላለን ወይስ አንችልም?” ብለው ለሚጠይቁት ጥያቄ መልስ ይሰጠን ይሆን? አንድ ሰው ኃጢያቱ ይቅር እንደተባለለት ያውቅ ይሆን? ወይስ ለማወቅ የፍርድ ቀን እስኪመጣ መጠበቅ ይኖርበታል? ይህን ወሳኝ ጥያቄ ለመመለስ እስከዚያን ቀን መቆየቱ አለመታደልና በጣም አደገኛ ውሳኔ ነው፡፡ አዎን፤ የፈለገ ሰው ማወቅ ይችላል፡፡ ጌታም ስለመዳናችን እርግጠኛ እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ “እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ” (ማቴ. 11፥28) እያለ ጥሪውን እያቀረበልን ነው፡፡ በዮሐ.3፥16 “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን (ኃጢያተኛውን፤ ሁሉንም) እንዲሁ ወዶአልና” ሲል ይነግረናል፡፡ ሰው ሁሉ ከፍጥረቱ ኃጢያተኛ በመሆኑ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ከማድረግ ጎድሏል፡፡
ህይወት እንደ ጉዞ መሆኑን ታውቅ ነበር? የህይወት ጉዞ ወደ ሁለት ቦታ የሚያደርሱ ሁለት ጎዳናዎች አሉት፡፡ በየትኛው መንገድ ላይ ለመጓዝ መምረጥና መወሰን የአንተ ነው፡፡ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ልጅ ሲወለድ የህይወትን ጉዞ ይጀምራል፡፡ በሰማይ የሚኖር አምላክ ለታዳጊ ልጆች ልዩ መንገድን ያደርጋል፡፡ ይሄ መንገድ የየዋህነት፣ እራስን ወደ ማወቅ የሚያመጣ መንገድ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ላይ እናትና አባት ለልጆች ስለ ህይወት በማስተማር መሪዎች ናቸው፡፡
የሰው ልጅ ቅዱስ በሆነው በእግዚአብሔር ፊት በኃጢአቱ ወንጀለኛ ሆኖ በመገኘቱ ሞት እንደተፈረደበት ታውቃለህ? ከዚህ የዘላለም ሞት ፍርድ አምልጦ ለዘላለም ይድን ዘንድ የእግዚአብሔርን ምህረት መቀበል አለበት፡፡ ከዘላለም ሞት አንፃር ምህረት ማለት እግዚአብሔር የሰው ልጅ ሊቀበል ለሚገባው ፍርድ ይቅርታን ሲያደርግ ነው፡፡ ምንም እንኳ ድነት ነጻ የማይከፈልበትና በስራችን የምናገኘው ባይሆንም እግዚአብሔር ግን ምህረቱን ለሰው ልጅ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አይደለም የሰጠው፡፡ እግዚአብሔር ምህረት የሚደርግበት ቅድመ ሁኔታ ንስሐ ነው፡፡
የዮሐንስ ወንጌል 10፡ 1-18 አንድ ሰው ሲጠራህና የሚጠራህ ሰው ድምጽ ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ ለማወቅ ግራ ተጋብተህ ታውቅ ይሆን? ወይም ብዙ ጫጫታ መካከል ከመሆንህ የተነሳ የሚጠራህን ሰው ድምጽ ለመስማት ተቸግረህ ታውቅ ይሆን? አድምጥ! አንድ ድምጽ እየጠራህ ነው፡፡ አዎ አንተን! አንተ ማን ነህ? ስምህ ማን ነው? ከየት ነው የመጣኸው? የት ነው ምትኖረው? ወዴትስ እየተጓዝክ ነው? የምትኖርበትን አካባቢ ስም ታውቃለህ፡፡ ድነገትም ከምትኖርበት አካባቢ ርቀህ ተጉዘህ አታውቅ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የምትኖርበት አካባቢ የአንድ አገር አካል፤ አገራት ደግሞ የአለም አካል እንደሆኑ ታውቃለህ;፡፡
ሁሉም ሰው ይህንን “እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል?” የሚለውን ጠቃሚ ጥያቄ እራሱን ሊጠይቅ ይገባዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ድነናል ብለው ቢያምኑም ኢየሱስ ግን ሲናገር “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም” (ማቴዎስ 7፥21) ብልዋል፡፡ ድነትን ለማግኘት ክርስቶስ ኃጢአታችንን ይቅር እንደሚለን ማመን አስፈላጊ ነው፡፡ ከዛም ኃጢአታችንን መናዘዝ፣ በቅድስና መኖርና አንዳችን አንዳችንን በመውደድ በፍቅር ልንኖር ይገባል፡፡ በዚህ ዘመን የተለያዩ ኃይማኖቶች የተለያዩ ትምህርቶችን የሚያስተምሩ ሲሆን ሊጠየቅ የሚገባው መሰረታዊ ጥያቄ ግን “እውነት የትኛው ነው?” የሚለው ጥያቄ ነው፡፡
ዛሬ በዓለማችን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ልባቸው የታወከና የተጨነቀ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ምክንያቱ ምንም ቢሆን ምን እግዚአብሔር አዋቂ አማላክ እንደሆነ ልናምን፣ የተጨነቁ ልቦች ወደ እርሱ እንዲመጡ ጥሪውን እያቀረበና ሰላምን ሊሰጣቸው እየጠበቀ እንደሆነ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ይወድሀል፣ በልብህም ውስጥ ሊኖር ይሻል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሰው ልብ የሚያሳየው ሰው የሚወደው ነገር ሁሉ መቀመጫ የሆነውን ወይም “እውነተኛ አንተነትህ” ነው፡፡ የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የሚመነጩት ከልብህ ነው፡፡ ሰውን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በደስታና እያገለገለው በውቧ ኤደን ገነት እንዲኖር ነበር፡፡