ፈልግ በ FlexSearch
የሚፈልጉት ገጽ የለም ወይም ተንቀሳቅሷል።
በመጀመሪያ አለማችን ባዶ ነበረች፡፡ አሶች በባህር፣ ከዋክብት በሰማይ ላይ አልነበሩም፤ ባህርና ውብ አበቦች የሉም ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ነበር፡፡ እግዚአብሔር አስደናቂ እቅድ ነበረው፡፡ ውብ የሆነች አለምን ለመስራት አሰበ፡፡ እንዳሰበም ፈጠራት፡፡ እግዚአብሔር አለምን ሲፈጥር ከምንም ነው የሰራት፡፡ “…..ይሁን” አለ፤ ሆነም! ብርሀንን ፈጠረ፡፡ ወንዞችንና ባህርን፣ በሳር የተሸፈነች ምድርን፣ እንስሳትን፣ አእዋፋትንና ዛፎችን ሁሉ ሰራ፡፡ በመጨረሻ ሰውን ፈጠረ፡፡ ለፈጠረው ሰውም ሚስትን አበጀለት፡፡ ስማቸውም አዳምና ሔዋን ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሐር አዳምና ሔዋንን በጣም ይወዳቸው ነበር፡፡ ይኖሩበት በነበረበት በውቡ ገነት ሁልግዜ አመሻሹ ላይ እየመጣ ያነጋግራቸው ነበር፡፡ አዳምና ሔዋን እግዚአብሔር ከከለከላቸው ከአንድ ዛፍ በስተቀር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዲበሉ ተፈቅዶላቸው ነበር፡፡
ሰላም፤ ለአገራችን፣ ለቤታችን በተለይም ለልባችንና ለአእምሮአችን ሰላም የት ይገኛል? በሰዎች ዘንድ የሰላም የጥም ጩኸት ለዘመናት ሲያስተጋባ ኖርዋል፤ በተለይም ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደ አውሎ ንፋስ እየተናወጠችና ለአስደንጋጭ ክስተቶች ተጋላጭ እየሆነች በመጣች ቁጥር የሰላም ጉጉት ጩኸት ጎልቶ ይሰማል፡፡ ያንተስ የልብህ ጥማት ይሄ ነው? አለመርካትና ሁከት በነገሰበት ዓለም ውስጥ ሁሉን የሚያስንቅ ውስጣዊ ፀጥታን ማግኘት ትፈልጋለህ?
ህይወት እንደ ጉዞ መሆኑን ታውቅ ነበር? የህይወት ጉዞ ወደ ሁለት ቦታ የሚያደርሱ ሁለት ጎዳናዎች አሉት፡፡ በየትኛው መንገድ ላይ ለመጓዝ መምረጥና መወሰን የአንተ ነው፡፡ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ልጅ ሲወለድ የህይወትን ጉዞ ይጀምራል፡፡ በሰማይ የሚኖር አምላክ ለታዳጊ ልጆች ልዩ መንገድን ያደርጋል፡፡ ይሄ መንገድ የየዋህነት፣ እራስን ወደ ማወቅ የሚያመጣ መንገድ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ላይ እናትና አባት ለልጆች ስለ ህይወት በማስተማር መሪዎች ናቸው፡፡