ትራክቶች
ክፍሊቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ” (ራእይ 20፥12) የሚል ጥቅስን እናነባለን፤ ይህም እግዚአብሔር የእያንዳንዳችንን ሕይወት መዝግቦ እንደሚያስቀምት ማስረጃ ነው፡፡
ዛሬ በዓለማችን ላይ በተለያዩ ምክንያቶች ልባቸው የታወከና የተጨነቀ ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ ምክንያቱ ምንም ቢሆን ምን እግዚአብሔር አዋቂ አማላክ እንደሆነ ልናምን፣ የተጨነቁ ልቦች ወደ እርሱ እንዲመጡ ጥሪውን እያቀረበና ሰላምን ሊሰጣቸው እየጠበቀ እንደሆነ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ይወድሀል፣ በልብህም ውስጥ ሊኖር ይሻል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የሰው ልብ የሚያሳየው ሰው የሚወደው ነገር ሁሉ መቀመጫ የሆነውን ወይም “እውነተኛ አንተነትህ” ነው፡፡ የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የሚመነጩት ከልብህ ነው፡፡ ሰውን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በደስታና እያገለገለው በውቧ ኤደን ገነት እንዲኖር ነበር፡፡
እኔ አንድ ወዳጅ አለኝ፡፡ እርሱ ከወዳጆቼ ሁሉ ይልቅ የቅርብ ወዳጄ ነው፡፡ እርሱ በጣም ደግና እውነተኛ ስለሆነ አንተም እንድትተዋወቀው እፈልጋለሁ፡፡ ስሙ ኢየሱስ ይባላል፡፡ እርሱ የአንተም ወዳጅ መሆን ስለሚፈልግ በጣም ድንቅ ነገር ነው፡፡ ስለ እርሱ ልንገርህ፡፡ የእርሱን ታሪክ ከመጽሐፍ ቅዱስ እናነባለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እውነትና የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ አለምና በአለም ውስጥ ያለውን ሁሉ የፈጠረ እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ የሰማይና የምድር አምላክ ነው፡፡ እርሱ ሕይወትንና እስትንፋስን ለሁሉም ይሰጣል፡፡
ሰላም፤ ለአገራችን፣ ለቤታችን በተለይም ለልባችንና ለአእምሮአችን ሰላም የት ይገኛል? በሰዎች ዘንድ የሰላም የጥም ጩኸት ለዘመናት ሲያስተጋባ ኖርዋል፤ በተለይም ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደ አውሎ ንፋስ እየተናወጠችና ለአስደንጋጭ ክስተቶች ተጋላጭ እየሆነች በመጣች ቁጥር የሰላም ጉጉት ጩኸት ጎልቶ ይሰማል፡፡ ያንተስ የልብህ ጥማት ይሄ ነው? አለመርካትና ሁከት በነገሰበት ዓለም ውስጥ ሁሉን የሚያስንቅ ውስጣዊ ፀጥታን ማግኘት ትፈልጋለህ?
ሌባ ሳይታሰብ በሌሊት እንደሚመጣ ጌታም እንዲሁ በድንገት ይመጣል (2ኛ ጴጥሮስ 3፡19)፡፡ የጌታ የመምጫ ጊዜ ቅርብ እንደሆነ ለምን እናምናለን? በዙሪያህ እየሆነ ያለውን ስትመለከት፤ ምን ያሳስብሀል?